በየዓመቱ የካቲት 23 ቀን የሚከበረው ገድላዊውና ታሪካዊው የዓድዋ ጦርነት የድል በዓል እንደሁሌው ዘንድሮም ከዓድዋ እስከ አዲስ አበባ፣ ሌሎች አካባቢዎችን ጨምሮ በልዕልና ተከብሯል፡፡ ኢትዮጵያ በጣሊያን ላይ የተቀዳጀችው፣ ነጮች ለጥቁሮች እጅ የሰጡበት ታላቁን የድል በዓል ለማክበር በነያሬድ ሹመቴና መሐመድ ካሳ በ2006 ዓ.ም. የተወጠነው የጉዞ ዓድዋ አባላት፣ ከአዲስ አበባ እስከ ዓድዋ 1000 ኪሎ ሜትር ግድም በእግር ተጉዘው ማክበር ከጀመሩ ሰባት ዓመት ሞልቷቸዋል፡፡ ፎቶዎቹ የጉዞውን ከፊል ገጽታ ዓድዋ ከተማ እስከደረሱበት ያሳያሉ፡፡ ፎቶ ከያሬድ ሹመቴ ፌስቡክ ገጽ |
የዱር እንስሳት በአንድነት ፓርክ
የዱር እንስሳት በአንድነት ፓርክ በቀደመው ዘውዳዊ ዘመን፣ ታች ግቢ ይባል የነበረው ታላቁ ቤተ መንግሥት ዘዳግማዊ ምኒልክ፣ በቅርቡ በመንግሥት በተደረገለት የማሻሻልና የማዘመን ሥራ የዱር እንስሳት ፓርክ ባለቤት...
ተጨማሪ ያንብቡ