መድሀኒት የለሽ የሆነውንና ዓለምን እያዳረስ የሚገኘውን ኮሮና ቫይረስ (ከቪድ19) ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል፤ ዜጎች ካንዱ ክልል ወደሌላኛው ክልል ወይም በአንድ ክልል ውሰጥ በሚገኙ ከተሞች ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ የክልል መንግስታት እየጣሉ ስላለው እግድ ቆም ብለው ሊያስቡና ጥንቃቄ ሊያድርጉ አንደሚገባ እየተነገረ ነው። መንግስታቱ እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ ወይም እርምጃ፤ ከኮረና ቫይረስ ጋር የተያያዘና የቫይረሱ ስርጭት ተስፋፍቶ ሕዝባቸው እንዳይጎዳ አስቀድሞ ለመከላከል ቢሆንም ፤ ሙሉ ለሙሉ ዝግት አድርጎ እነዳይገቡ ወይም እንዳይወጡ ማድርግ ብቻ ሳይሆን ፤ እገዳውን ተከትሎ ሊመጡ የሚችሉትን ነግሮቸንም ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት ተብሏል። አብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ኑሮውን የሚመራው በቀን ውስጥ ተንቀሳቅሶ በሚያገኘው ገቢ ከመሆኑ አንፃር፤ እንዳይንቀሳቀስና በር ዘግቶ እንዲቀመጥ ክልከላ ሲጣልበት፤ ቢያነስ የእለት ጉርሱን የሚያገኝበት ሁኔታ ሊመቻችለት ይገባል። መግቢያ መውጫውን ዘግቶ በቤት ውስጥ እንዲቆይ ማድረግ ተገቢ ካለመሆኑም በተጨማሪ ለሌላ ጉዳት ሊዳርገው ስለሚችል አስፈላጊው ቅድመ ሁኔታዎች ሊሟሉለት ይገባል። ኢትዮጵያውያን በዚህ ክፉ ቀን እርሰ በርስ መደጋገፍ፣ ትንሽ ያለው ምንም የሌለውን እንዲዲግፈውና መንግስትም በተቻለው አቅም በተለይም የደሀ ደሀ የሚባሉ ወገኖችን የሚደግፍበትን መንገድ ማመቻቸት አለበት። ከተለያዩ አገሮች ወደኢትዮጵያ የሚገቡትን ወገኖች ለአስራ አራት ቀናት በለይቶ ማቆያ ቦታ ለማቆየት ለሚያስፈልገው ወጪ፤ ኢትዮጵያውያን ያለምንም ስስት እየተረባረቡ የሚያደርጉትን ተሳትፎ ምንም ዓይነት ገቢ ለሌላቸውና በቤታቸው ተቀምጠው ይህንን ግዜ እንዲያሳልፉ ግዳጅ ለተጣለባቸው ወገኖችም ጭምር የሚደርሱበትን መንገድና ሁኔታዎችን መንግሥት ማመቻቸት አለበት። በተለይ ከክልል ክልል በሚደረጉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ በህይወት ለመቆየት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን መቀያየር የሚቻልበት ሁኔታ እንዲፈጠር፤ የፌዴራልም ሆነ የክልል መንግስታት ጠንክረው መሥራት አለባቸው።
በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ብዛት ሥጋት ፈጥሯል
አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ -19) ተጠቂዎች ቁጥር ከመቶ በላይ መድረሱ በተለይ በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ ሥጋት ፈጥሯል፡፡ አብዛኛዎቹ የቫይረሱ ተጠቂዎች ከአዲስ አበባና ከሶማሌ ክልል...
ተጨማሪ ያንብቡ