የሚኒስትሮች ምክርቤት ለ2013 በጀት ዓመት 476,012,952,445 ብር ረቂቅ በጀት እንዲያጸድቅለት፡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ግንቦት 29 ቀን 2012 ዓ.ም ውሳኔ አሳልፎ ልኳል።
ምክር ቤቱ ለፌደራል መንግስት መደበኛ ወጪ 133,321,561,063 ብር፣ለካፒታል ወጪዎች 160,329,788,483 ብር፣ለክልሎችየሚሰጥ ድጋፍ 176,361,602,899 ብር እና ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈፀሚያ ድጋፍ 6,000,000,000 ብር ፡ በድምሩ 476,012,952,445 ብር ረቂቅ በጀት አጽድቆ ለምክር ቤቱ ልኳል።
ምንም እንኳንየሚኒስትሮች ምክር ቤት ዓመታዊ በጀትን በረቂቅነት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲልክ ውይይትና ክርክር ተደርጎበት ከፍ ብሎ ወይም ተቀንሶ የሚፀድቅ ቢመስልም፣ ከልምድ እንደሚታወቀው ፖርላማው የቀረበለትን በጀት እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።