ከኮረና ቫይረስ ጋር ተያይዞ በቤት ውስጥ እንዲቆዩ የተደረጉ ሕፃናት ቤተሰቦቻቸው እንደተደፈሩ ቢነገርም፡ ምንም ዓይነት የክስ ፋይል አለመከፈቱን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል።
በሁለት ወራት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ101 በላይ ሕፃናት በቤተሰቦቻቸው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንደተፈፀመባቸው የአዲስ አበባ ሴቶች፣ወጣቶችና ሕፃናት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አልማዝ ኃይሌ ገልፀው ነበር።
ተደፍረዋል ስለተባሉት ወንድና ሴት ሕፃናት ኃላፊነቱን ወስዶ ጉዳዩን ወደ ፖሊስ በመውሰድ እንዲጣራ ማድረግ ያለበት ቢሮው በመሆኑ ጉዳዩ ተዳፍኖ እንዳይቀር ሁሉም ኢትዮጵያውያን መረባረብ እንዳለባቸውም ግፊት እየተደረገ መሆኑን የሪፖርተር መጽሔት ለማወቅ ችሏል።