ፌደሬሽን ምክርቤት ከሕገመንግስት አጣሪ ጉባኤ የቀረበለትን ውሳኔ አጸደቀ
አፈጉባኤም መርጧል
የኢፌዴሪ ሕገመንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ በ 20 ቀናት ውስጥ ውይት በማድረግና የተለያዪ ሀሳቦችን ተቀብሎ “ሕገመንግስቱ ይተርጎምልኝ” በማለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በላከለት ጥያቄ መሰረት ተርጉሞ የላከለትን ውሳኔ የፌደሬሽን ምክርቤት ዛሬ ሰኔ 3ቀን 2012 ዓም አጽድቆታል። በመሆኑም የፖርላማውንና ሥራ አስፈጻሚን የሥራ ጊዜ እንዲራዘምና ምርጫም ኮሮና ቫይረስ ከቆመበት ጊዜ አንስቶ በአንድ ዓመት ውስጥ እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።
ምክር ቤቱ ሰኔ 1 ቀን 2012 ዓም በራሳቸው ፈቃድ ከኃላፊነታቸው በለቀቁት ወ/ኬሪያ ኢብራሄም ቦታ አፈጉባኤም ተሾሟል።
አደም ፉራን ወ/ሮ ኬሪያን ኢብራሔምን ተክተው የፌደሬሽን ምክርቤት አፈጉባኤ ሆነው ተመርጠዋል