የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት አባል አገራት በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ለመወያየት ተስማሙ።
አባል አገራቱ የፊታችን ሰኞ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 9:00 ሰዓት ላይ የቪዲዮ ኮንፈረንስ (Virtual meeting) ለማድረግ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ታውቋል። ሦስቱ ተደራዳሪ አገሮች ግብፅ፣ሱዳንና ኢትዮጵያ ስለ ህዳሴው ግድብ ለአባላት አገራቱ ስለግድቡ ማብራሪያ እንደሚሰጡም ታውቋል።