ማኀበረ ሰብ

ልውጥ ሕያዋን፡ የንትርክ ‘ዘሮች’

በሶፎንያስ ዳርጌ እና አባዲ ግርማይ ከዓመታት በፊት በሃረማያ ዩኒቨርሲቲ የዕፀዋት ማዳቀል (Plant breeding) የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች መካከል ሳይንሳዊ ሙግት የማድረግ ባህል ነበር። በየዓመቱ የድኅረ ምረቃ ተመራቂ ተማሪዎች በሁለት ቡድን ተከፍለው ይሟገታሉ። አንደኛው ቡድን “ልውጥ ሕያዋን (GMOs) ያላቸውን ጠቀሜታ በመደገፍ”፣ ሁለተኛው ቡድን ደግሞ በተቃራኒው በመቃወም ይከራከራሉ፡፡ በሁለቱም ወገን የሚደረጉ ሳይንሳዊ ሙግቶች የሚዳኙት ከተለያዩ የሙያ መስኮች በመጡ የሙግቱ ታዳሚዎችና በመምህሮቻቸው ነበር፡፡ ይህ...

ተጨማሪ ያንብቡ

ትውልደ ኢትዮጵያ የእስራኤል ሚኒስትሮች

በወርኃ ግንቦት ከዓመት በፊት “ከኔሴት” የሚባለው የእስራኤል ፓርላማ አዲስ የተመረጡ የምክር ቤት አባላትን ቃለ መሐላ ለማስገባት ተሰብስቧል፡፡ እንደራሴዎቹና ታዳሚ እንግዶች ወደ አዳራሽ እየዘለቁ ነው፡፡ ከሚገቡት መካከል ኢትዮጵያውያት ይሁዲዎች በባህል አልባሳት ተውበውና ተጊጠው በመግባት ላይ ናቸው፡፡ ከነርሱም መካከል በዕድሜ ገፋ ያሉ አንዲት እናት ዘመናዊ ከዘራ ይዘው ዋናውን በር አልፈው ሊገቡ ሲል አንድ ከአርባ ዓመት ዕድሜ ያልደረሱ፣ አርባ ፈሪ ላይ ያሉ ወጣት...

ተጨማሪ ያንብቡ

ሰኔ 14 ቀን የሚጠበቀው ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ

ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ የፊታችን እሑድ ሰኔ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ማለዳ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአብዛኛው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ እንደሚታይ ይጠበቃል፡፡ ግርዶሹ በአፍሪካ ዕምብርት ሲጀምር በጨረቃ ጥላ ሥር የሚያልፉት አገሮች ኮንጎ ዴሞክራቲክ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኢትዮጵያና ኤርትራን ሲሆኑ፣ ሌሎች አካባቢዎች የሚያዩት ከፊል ግርዶሽ ነው፡፡ ቀለበታዊው ግርዶሽ የሚታየው ጨረቃ በፀሐይና በምድር መካከል ስትሆንና  ፀሐይ ሙሉ በሙሉ ተጋርዳ ብርሃን መስጠት ሳትችል በሚፈጠር ክስተት...

ተጨማሪ ያንብቡ

ከኮረና ቫይረስ ጋር ተያይዞ በቤት ውስጥ እንዲቆዩ የተደረጉ ሕፃናት ቤተሰቦቻቸው እንደተደፈሩ ቢነገርም፡ ምንም ዓይነት የክስ ፋይል አለመከፈቱን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል።

ከኮረና ቫይረስ ጋር ተያይዞ በቤት ውስጥ እንዲቆዩ የተደረጉ ሕፃናት ቤተሰቦቻቸው እንደተደፈሩ ቢነገርም፡ ምንም ዓይነት የክስ ፋይል አለመከፈቱን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል። በሁለት ወራት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ101 በላይ ሕፃናት በቤተሰቦቻቸው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንደተፈፀመባቸው የአዲስ አበባ ሴቶች፣ወጣቶችና ሕፃናት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አልማዝ ኃይሌ ገልፀው ነበር። ተደፍረዋል ስለተባሉት ወንድና ሴት ሕፃናት ኃላፊነቱን...

ተጨማሪ ያንብቡ

ዕድሜ ጠገቡ የኢትዮጵያ ዝሆን ሕይወት አለፈ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኘው ጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ይኖር የነበረው ዕድሜ ጠገቡና ዝነኛው ዝሆን፣ ግንቦት 13 ቀን 2012 ዓ.ም. ሕይወት ማለፉን የፓርኩን ኃላፊ ጠቅሶ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡    “ሹሉሬ” በሚል ቅፅል ስም የሚታወቀው ዝሆን የሞቱ መንሥኤ እርጅና መሆኑን ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ሚዲያው ገልጿል፡፡ ሟቹ ዝሆን አድፍጦ የሚያጠቃ ግዛቱን ያስጠብቅ ስለነበረ በኮንታኛ ቋንቋ “ሹሉሬ” የሚል ስም በኅብረተሰቡ እንደተሰጠው ይወሳል፡፡  ሹሉሬ ከ50...

ተጨማሪ ያንብቡ

ከጦር ጀግኖች ባሻገር . . .

ዲፕሎማትና የእንግሊዝኛ አስተርጓሚ የነበሩት የቅርብ ወዳጃቸው አቶ ጳውሎስ መንአመኖ፣ በእርሳስና በቀለም የተጻፉትን ወረቀቶች ሲሰበስቧቸውና በ1914 ዓ.ም. ለልዑል አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኰንን (የወደፊቱ አፄ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት) “ለኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ የሚጠቅም ነገር አላቸው” ብለው እንዲታተም በልመና መልክ ደብዳቤ ሲልኩላቸው፣ በ1940ዎቹ ተፈጠረ የተባለውን በመዋቅራዊ  ችግሮች  ላይ  ያተኮረ  የኢኮኖሚ አተናተን (Structural  economics)፣ በተለይም የፕሬቢሽ እና ሲንገርን ሥራዎች፣ ከፍ ሲል ደግሞ የልማት ምጣኔ...

ተጨማሪ ያንብቡ

እንስሳትን በሰላም የማሰናበት እንቅስቃሴ

በብዛት የአዲስ አበባ ጥግ ላይ ቆመው ሲተክዙ ይታያሉ፡፡ የሆነ ነገር በመጠበቅ ላይ ያሉም ይመስላሉ፡፡ እንቅስቃሴ የላቸውም በዚያው ተፈጥረው እዚያው ኖረው እዚያው የሚሞቱ ነው የሚመስሉት፡፡ ነገር ግን ሀቁ ሌላ ነው፡፡ ብዙ አገልግሎት ሰጥተውና ብዙ ተጎድተው የተጣሉ ናቸው፡፡ አብዛኞቹ እንዲያውም ዝንብ እንደወረራቸው ነግቶ ይመሽባቸዋል፡፡ ፈረሶች ከቤት እንስሳት መሀል ይጠቀሳሉ፡፡ ሰፊ አገልግሎት በመስጠትም ይታወቃሉ፡፡ በተለይ በገጠራማው የኢትዮጵያ ክፍል ላይ መሠረት ናቸው፡፡ ለመጓጓዣና ለስፖርታዊ...

ተጨማሪ ያንብቡ

ዓድዋ – “የአንድነታችን ድርና ማግ”

ዓድዋ - “የአንድነታችን ድርና ማግ” «ሃያ ሺሕ ያህል ወታደሮች ያሉበት የአውሮፓ ጦር በአፍሪካ ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ተሸነፈ፡፡ በእኔ እምነት መሠረት በዘመናችን ታሪክ ውስጥ እንደ ዓድዋው ያለ ጦርነት የለም፡፡ 25,000 ሰዎች በአንድ ቀን ጀንበር የሞቱበትና የቆሰሉበት ነው፡፡ ፖለቲካና ታሪክ አበቃ፡፡ ሀበሾች አደገኛ ሕዝቦች መሆናቸው ከኦሪት ዘፍጥረት ጀምሮ ተጽፎላቸዋል፡፡ የእኛ ዓለም ገና ቶር እና ኦዲዮን በሚባሉ አማልክት ሲያመልክ በነበረበት ጊዜ ሀበሾች ክርስትናን...

ተጨማሪ ያንብቡ

ታሪክና ትርክትን ለአገረ መንግሥት ግንባታ እንዴት እናውለው?

መንግሥታትና መሪዎች አገርን ለመገንባት ከሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች መካከል ረቂቅ ወይም ተምሳሌታዊ (ሲምቦሊክ) ጉዳዮች ውስጥ አገራዊ ትርክቶችና የጋራ ትውስታዎች ይገኙበታል፡፡ በእነዚህ ውስጥ ደግሞ ታሪክ አለ፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ማኅበራዊ ቅራኔዎችንና የታሪክ ጠባሳዎች እየተለቀሙ አቃቃሪና ግጭት ጠሪ ትረካዎች (በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጭምር) በቆስቋሾች እየተደረቱና እየተወረወሩ ለቁርሾ ማወራረጃና ለሥልጣን ሸኩቻ መሣሪያ እየተደረገ በመሆኑ የኢትዮጵያ ታሪክ ለአገረ መንግሥት ግንባታ ያለው ተፅዕኖ አነጋጋሪነቱ እየጐላ መምጣቱ...

ተጨማሪ ያንብቡ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየምን ምን አጠፋው?

የሰው ዘር አመጣጥ ሙዚየም ዕቅድ እምን ደረሰ? ከካዛንቺስ ስድስት ኪሎ ተሳፋሪዎችን ይዞ ሚኒባስ ታክሲ እያመራ ነው፡፡ በሚያዝያ 27 አደባባይ በኩል አራት ኪሎንና ቅድስት ማርያምን ሲያልፍ ከተሳፈሩት ሁለቱ ወጋቸውን ቀየሩ፡፡ ‹‹አንተዬ ብሔራዊ ሙዚየም ስሙ ተቀይሯል፣ የለም እየተባለ ነው›› ይለዋል፡፡ ‹‹ምን እያልክ ነው ይኸው በሩ ላይ ያለው ሰሌዳ ‹የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም› ይላል አይደለም እንዴ?›› ይመልሳል ሌላው፡፡ ‹‹የተንቀሳቃሽ ቅርስ ምናምን  ነው ያሉት ስሙን...

ተጨማሪ ያንብቡ

በብዛት በመነበብ ላይ ያሉ መጣጥፎች

Follow us on Facebook