ኮሮና ቫይረስ እየደቆሳቸው ያሉ አነስተኛና ጥቃቅን ነጋዴዎች
በቻይናዋ ሁቤ ግዛት ውሃን ከተማ በታኅሣሥ ወር የተቀሰቀሰው የኖቭል ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ባለፉት አራት ወራት ውስጥ እንደሰደድ እሳት ተስፋፍቶ ከ200 በላይ አገሮችን አዳርሷል፡፡ እስካሁን በዓለም ዙሪያ በቫይረሱ ከአራት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሲጠቁ፣ ከ290,000 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ወረርሽኙ በቀላሉ የሚሰራጭና ክትባትም ሆነ መድኃኒቱ እስካሁን በወጉ ያልተገኘለት በመሆኑ፣ ቫይረሱ እያስከተለ ካለው የጤና ቀውስ ባሻገር፣ የሰው ልጆችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በመግታት በዓለም...