ጥበብ እና ባህል

እውነትና ንጋት… (የመጽሐፍ ቅኝት)

እውነትና ንጋት… (የመጽሐፍ ቅኝት) በግርማ አውግቸው ደመቀ ረዘነ ሃብተ። 2019። ደም የተከፈለበት ባርነት፤ የኤርትራ አብዮት ህልሞችና ውድቀት። ትሪንተን፤ ዘ ሬድ ሲ ፕረስ። 314 ገፆች፣ 5.5X8.5”፣ $30.00። “በግብፅ ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት የኤርትራ ነጻ አውጪ ድርጅት (ጀብሃ) እ.ኤ.አ. በ1960 ከተመሰረተ በኋላ በ1961 የትጥቅ ትግል ተጀመረ። ሃይማኖታዊ እና ዓረባዊ አጀንዳ ለማስፈጸም በዓረብ መንግስታት ቀጥተኛ ድጋፍ የተመሰረተው ጀብሃ መሪ የነበረው ኢድሪስ መሐመድ አደም በተመሳሳይ...

ተጨማሪ ያንብቡ

“ኢትዮጵያ በኢየሩሳሌም” ዓውደ ጥናት ሊካሄድ ነው

በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን ጋር በመተባበር “ኢትዮጵያ በኢየሩሳሌም” በሚል ርዕስ ያዘጋጀው ዓውደ ጥናት (ዌብናር ሲምፖዚየም) ሰኔ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደሚጀመር አስታወቀ፡፡ ኤምባሲው ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ዓውደ ጥናቱ የሚካሄደው በዙም በጉግል ስብሰባ መስመሮች ሲሆን፣ ተባባሪዎቹ ምሁራን የተወጣጡት ከቴልአቪቭ ዩኒቨርሲቲ፣ ከሂብሪው ዩኒቨርሲቲ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ከባዛሌል አካዴሚ ነው፡፡ ቀዳሚው ዓውደ ጥናት የሚጀመረው ረቡዕ ሰኔ 10 ቀን ከቀኑ 10 ሰዓት...

ተጨማሪ ያንብቡ

ድል አብሳሪዎቹ ጀግኖች ኢትዮጵያውያት

“በሳል፣ በጉንፋን የምትሞተውን ሞት ከሩቅ አገር እኛን ለማጥቃት ለመጣው ጠላታችን ባገርህና በርስትህ በቤትህ ላይ ሁነህ መመከት አቅቶህ ላገርህ ኢትዮጵያ ሞት ብትነፍጋት፣ ደምህንም ሳታፈስ ብትቀር በፈጣሪህ የምትወቀስበት በዘርህ የምትረገምበት ነውና የተለመደ የጀግንነት ልብህን ሳታበርድ፣ ወደፊት የሚቆይህን ታሪክህን እያሰብህ ጠንክረህ ለመዋጋት ቆርጠህ ተነሣ” ይህ ከላይ የሰፈረው ኃይለ ቃል፣ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ከሰማንያ አራት ዓመታት በፊት ፋሺስት ጣሊያን በሰሜን በኩል መረብን ተሻግሮ...

ተጨማሪ ያንብቡ

ዓባይ የህልውና ዋስትና የሕይወት ኅብስተ መና

“በመልክዓ አፍሪቃ ላይ፣ እንደ አጎበሩ የወላድ እናት ጡቶች ጉብ ብላ፣ ለልምላሜና ለሥልጣኔ ምክንያት የሆነ ማየ ሐሊቧን ወደታች እየረጨች በመኖሯ፣  ለለጋሥነቷ እንከን አይወጣላትም፡፡ ይሁን እንጂ፣ ነባር ዘመናት ተለውጠው በአዲስ ዘመኖች በተተኩ ቁጥር፣ በአዲሱ ዘመን የሚገኝ ትውልድ ሁሉ ከአዲስ ፍላጎቶች ጋር የሚመጣ በመሆኑ፣ ነባር ልግሥናም  ይዘቱን መቀየር ግድ ይሆንበታል፡፡ የአዲሱ ትውልዳችን አስተሳሰብና ዝንባሌ እጅግ ደርቆ የገረረም ባይሆን፣ እርጥብ አይደለም፡፡ እንደነዓባይ...

ተጨማሪ ያንብቡ

ፖለቲካ እና ኩሽ ኩሸቲክ

ክፍል ፪ የኩሽ ነገድ በመፅሀፍ ቅዱስ እሳቤ ፖለቲካ እና ኩሽ ኩሸቲክ ክፍል ፩ በመፅሀፍ ቅዱስ ያለውን የኩሽ አገባብ በርካታ ስራዎች ሲመረምሩት ቆይተዋል። በሀገራችን እንኳ ሩቅ ሳንሄድ ኪዳነወልድ ክፍሌን (1948) እና ተክለፃዲቅ መኩሪያን መጥቀስ ይቻላል። የኤፍሬም ይስሐቅ (1980) ኩሽ፣ ጁዳይዝም እና ስሌቨሪ ‘ኩሽ፣ ይሁዲነት እና ባርነት’ የሚለው መጣጥፍ የኩሽን አገባብ በስፋት በመፅሀፍ ቅዱስና በድኅረ-መፅሀፍ ቅዱስ የአይሁድ እምነት ስራዎች ውስጥ የሚመረምር ነው።...

ተጨማሪ ያንብቡ

ፖለቲካ እና ኩሽ ኩሸቲክ

ክፍል ፩ ኩሽ በጥንታዊ አጠቃቀሙ ሕዝብን/ ነገድን ለማመልከት ሲውልም ይስተዋላል የኩሽና የኩሸቲክ ጉዳይ የፖለቲካ መነጋገሪያ ከሆነ ሰነበተ። እውነታውን መርምሮ ከማወቅ ይልቅ እዚህም እዚያም ለጊዜያዊ ፍጆታ በሚመስል የታሪክ መሠረት የሌለው ትርክት በዘፈቀደ ሲሰጥ ይስተዋላል። ይህን ጉዳይ ፈረንጆች ሳይቀሩ ታዝበውታል፣ “ዛሬ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች የኩሸቲክ ሕዝብ ከሴሜቲክ ሕዝብ በላይ የአገሪቱ ባለመብት እንደሆኑ አጥብቀው ያሰምሩበታል” (ብሬየር 2007:460)። ለዚህ ሦስት መሠረታዊ...

ተጨማሪ ያንብቡ

ለቅዱስ ያሬድ ሐውልት ማቆም ያለበት ማን ነው?

“ከእርሱ በፊትም ሆነ ከእርሱ በኋላ እርሱን የመሰለ አልተገኘም!”  የሚል ብሂል በግዕዝ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ የሠፈረለት የስድስተኛው ምዕት ዓመት የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ደራሲ፣ የዜማ ቀማሪ፣ ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ ግዕዙ “አልቦ እምቅድሜሁ ወአልቦ እምድኅሬሁ” ይለዋል፡፡ በብዙኃኑ ጎልቶ ከሚነገረው ከዜማው በተጨማሪ ሊወሱ ከሚገባቸው የቅዱስ ያሬድ ትሩፋቶች አንዱ ከሥነ ጽሑፍ ጋር የተያያዘው ነው፡፡ ከድንጊያ ላይ ጽሑፍ ወደ ብራና ላይ ጽሑፍ ሽግግር በተደረገበት ዘመነ አክሱም...

ተጨማሪ ያንብቡ

ሀበሻ ማን ነው?

ሀበሻ ማን ነው?         ሀበሻ ኢትዮጵያዊ ከሚለው ቃል ይልቅ በአጠቃቀም በህብረተሰቡ ዘንድ ስር የሰደደ ነው። በርካታ ሀገራዊ (ቁሳዊና ሀሳባዊ) ባህሎች በዚህ ቃል ቅፅልነት ሲገለፁ ይስተዋላል። ለዚህ አስረጅ፣ የሀበሻ ዶሮ፣ የሀበሻ ጎመን፣ የሀበሻ መድሀኒት፣ የሀበሻ ኩራት፣ የሀበሻ ተንኮል፣ የሀበሻ ምቀኝነት፣ ወዘተ. የሚሉትን አጠቃቀሞች መጥቀስ ይቻላል። ሀበሻ የሚለው ቃል ከህንድ እስከ አውሮፓ መላው አለም ኢትዮጵያን ለመግለፅ ሲጠቀሙበትም ቆይቷል። በህንድ፣...

ተጨማሪ ያንብቡ

በብዛት በመነበብ ላይ ያሉ መጣጥፎች

Follow us on Facebook